ቅን ሰው አቶ በቀለ ገርባ

ቅን ሰው አቶ በቀለ ገርባ

የኛ ኢትዮጵያውያን ነገር ሆኖ እንጂ ብዙ ሊነገርላቸው የሚገባ ምርጥ ሰዎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አሉ። ላመኑበት አላማ በርካታ አመታት በእስር የማቀቁ።

ከነዚህም መካከል እንደ 30 አመቱ አገዛዝ አሁንም በእስር ላይ ያሉት አቶ በቀለ ገርባ ቅን ትሁት እውቀት ያላቸው ምርጡ የኦሮሞ ፖለቲከኛ ናቸው።

አቶ በቀለ ገርባ ለኢትዮጵያ ህዝቦች በተለይ ደግሞ ለኦሮሞ ህዝቦች በደል ሲጮሁ በተደጋጋሚ እስር ቤት ገብተዋል። ተሰድበዋል ተገልለዋል ተወግዘዋል። አሁንም እንደዛው።

የኢህያዴግ መንግስት ብዙ ጊዜ በእስር እንዲማቅቁ አድርጓቸዋል። ይህ ሁሉ መከራ እና እስር ቢሰቃዩም ላመኑበት እምነት ግን እራሳቸውን ሰጥተዋል። በአላማቸውም ፀንተዋል።

አቶ በቀለ እስከ ዛሬ ድረስ በርካታ የዓመት በዓላቶችን በእስር ቤት አሳልፈዋል። ቤተሰቦቻቸው እንደ አባት በህይወት እያሉ ከጎናቸው አጥተዋቸዋል። ያሳዝናል።

ለመሆኑ አቶ በቀለ ለዚህ ሁሉ እስር እና እንግልት የዳረጋቸው ምንድነው ብላችሁ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ? በትክክል ሊጠየቅ የሚገባው ትልቅ ጥያቄ።

ብዙ የኦሮሞ ተወላጆች ወደ ትግል የሚገቡት ዋነኛ አላማቸው በኦሮሞ ላይ የሚደርስን ግፍ እና መገለል በመቃወም ነው። ለነፃነታቸው ሲሉ በደል በመቃወም።

ላለፉት ከ 125 አመታት በላይ ኦሮሞ በማንነቱ በብሄሩ በአመለካከቱ ተገሏል ተበድሏል በገዛ ሀገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥሯል ብለው ብዙ የኦሮሞ ታጋዮች ያምናሉ።

አንዳንዶች እንደውም ሳይፈልጉ የኦነግ አባል በመሆን ኢትዮጵያዊነታቸውን በመካድ እኛ ኦሮሞአውያን እንጂ ኢትዮጵያ አይደለንም ብለው ጫካ እስከመግባት ደርሰዋል።

ጥቂት የማይባሉ ደግሞ ኢትዮጵያዊነታቸውን አምነው በብሔር ደግሞ ኦሮሞነታቸውን ተቀብለው የሚደርስባቸውን መገለል እና ጭቆና በመታገል ላይ ይገኛሉ።

አቶ በቀለም ከነዚህ ሰላማዊ ታጋዮች መካከል አንዱ ናቸው። ይሄንንም ትግላቸውን የጀመሩት ከብዙ አመታት ጀምሮ ቢሆንም ላለፉት 10 አመታት ግን በልዩ መልኩ ታግለዋል።

በዚህም አመለካከታቸው የኦህዴድ ባለስልጣናት በእስር እንዲማቅቁ ፈርደውባቸዋል። ያለምንም ፍርድ እና ጥፋት ብዙ አመታትን በእስር ቤት አሳልፈዋል። ተሰቃይተዋል።

ከ3 አመት ወዲህ ደግሞ የታገሉለት አላማ ፍሬ አፍርቶ ወደ ነፃነት ቢያመጣቸውም በድጋሚ ስልጣን ላይ ያለው የብልፅግና መራሹ ቡድን አስሯችዋል።

ሌላው የአቶ በቀለ ምርጡ ባህሪያቸው የይቅርታ ልባቸው ሁሌም ያስገርመኛል። ለ 27 አመት ስልጣን ላይ የነበረው አስሯቸው ግን ቂም አልያዙም ነበር።

ይሄን እረስተው እና ትተውት መቀሌ ድረስ በመሄድ የሰላም አማራጮችን በማድረግ ከትግራይ ባለስልጣናት እና ህዝብ ጋር ይወያዩ ይነጋገሩ ነበር።

ይህ የሚያሳየው ምን ያህል በልባቸው ቅን እና ትሁት መሆናቸውን ነው።

About Author