ቲቢ ጆሹዋ ብዙ ጉዳት አድርሷል።

ቲቢ ጆሹዋ ብዙ ጉዳት አድርሷል።

ይሄን ንግግር የተናገራችው ታዋቂዋ የ ናይሄሪያ ጋዜጠኛ Sandra Ezekwesili በቲውተር የትስስር ገፅ ላይ ነው።

አያይዛም ስትናገር በርካታ ተከታዮቹን ሆስፒታሎችን እንዳይሞክሩ እና መድኃኒታቸውን እንዲተዉ አላስተማራቸውም?

በህመም ጊዜ ጤና ተቋማት ከሚሄዱ ይልቅ በእርሱ በኩል የተፀለየበትን የተቀደሰ ውሃው እና ዘይት ብቻ እንዲጠቀሙስ አላስተማረም?

የሚል ይዘት ያለው ቲውት አድርጋ በብዙ ሚዲያዎች የናይጄሪያ ጋዜጦች ታዋቂ ሰዎች እና ቲቢ ጆሽዋን በሚከተሉ ዘንድ መነጋገሪያ ሆናለች።

የሳንድራ ቲውት መነጋገሪያ የሆነው ደግሞ ብዙ ሰዎች ወደ ሆስፒታል እንዳይሄዱ ሲመክር የነበረው እንዴት ሆስፒታል ሄደ?በማለት ነው።

በህመማቸው ጊዜ ሀኪም እንዳያዩ ያደረገው ነብይ በራሱ ሲመጣበት ግን ተግባራዊ ሆኖ አልታየም ከመሞቱ በፊት ሆስፒታል ነበር ብላለች።

ስለዚህ ቲቢ ጆሽዋ በጣም ብዙ ጉዳት አድርሷል ዛሬ ሲሞት መልካም ነገሮቹን ብቻ ማውራት ሐቀኝነት የጎደለው ነው ጥፋትም ሰርቷል ብላለች።

ስለ ቲቢ ጆሽዋ ሲወራ መወራት ካለበት ሁለቱም ጎኑ ነው። በእርሱ ምክንያት ስለሞቱ ሰዎች ሀኪም ማየት ሲገባቸው ስላላዩ ሰዎችም መወራት አለበት።

ያልኩትን ብያለሁ ሰውየው እንደ መሪ ሃላፊነት የጎደለው በክርስቶስ ፈለግ ያልሄደ እና አገልግሎቱም መርዛማ እና መበዝበዝ ነበር ብላለች።

በተጨማሪም ስለ ቲቢ ጆሽዋ ስትናገር

የተናገርኩትን ሁሉ ትክክል ነው ንግግሬን ሞት አያጠፋውም በኖረበት ወቅት ስለ እርሱ ስናገር ምንም ጥሩ ነገር አልነበረኝም ስለሞተ አሁን አልጀምርም ስትልም ጽፋለች።

ቲቢ ጆሽዋ በመላው አለም በርካታ ተከታዮች ያሉት ነብይ ሲሆን በኢትዮጵያም ሺህ ዎች የሚከተሉት የእግዚያብሄር ሰው እንደሆነ የሚያምኑ አሉ።

በተቃራኒው ደግሞ ዘይት ቸርቻሪ ሀሰተኛ ነብይ አጭበርባሪ ሰው ነው ብለው የሚያምኑ በርካቶች ናቸው። ያም ሆነ ይህ ቲቢ ጆሽዋ ድንገት አርፏል።

About Author