የመንግስት ሀሰት ሲጋለጥ በማስረጃ

የመንግስት ሀሰት ሲጋለጥ በማስረጃ

ከ አንድ ሳምንት በፊት የመንግስት ሚዲያዎች አንድ ዘገባ ለህዝብ አቅርበው ህዝቡም መንግስትን አምኖ ሲቀባበለው ነበር። ግን እውነታው ምንድነው?

በመንግስት ልሳን የቀረበው እንዲህ በሚል ነበር ፤ አገሪቱን የሽብር ቀጠና ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የአሸባሪው ህዋሃት ቡድን አባላት ተያዙ።

በጅቡቲ መንግስት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ እና መንግስት ከጅቡቲ ባለስልጣናት ጋር በመተባበር አስሮ አዲስ አበባ እንዳመጣቸው ነበር በዜና መልኩ የዘገቡልን።

ለመሆኑ እውነታው የቱጋር ነው? ጦርነት በተጀመረ ሰአት በሰሜን ዕዝ ላይ ጭፍጨፋ አድርገው ወደ ጅቡቲ አመለጡት የተባሉት 3 ሰዎች እነማናቸው?

የህግ ማስከበር ዘመቻ የተባለው ጦርነት ሲጀመር እነዚህ ሰዎች የት ነበሩ? በምን ስራላይ ተሰማርተውስ ነበር? እንዴት አሸባሪ ሊባሉስ ቻሉ በምን ማስረጃ?

በስም ከተጠቀሱት መካከል 1ኛ ሀብቶም ገብረስላሴ 2ኛ. መሰለ ታመነ እሼቱ እና 3ኛ. ኮነሬል መሀመድ በሪሁ ኑር ይገኙበታል። ዛሬ እኔ ስለ አንዱ መርጃ ልስጣችሁ።

ስለ ሀብቶም ገብረስላሴ

ሀብቶም እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከ 2007 ዓ/ም ጀምሮ በጅቡቲ የአምባሳደሩ ሹፌር በመሆን ከአዲስ አበባ በአምባሳደር ሱሌማን ደደፎ የተመረጠ ልጅ ነው።

ቀደም ሲል ሀብቶም በአምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ቤት በሹፍርና ሲያገለግል ካሳየው ታማኝነት እና ትህትና አንፃር አምባሳደሩ ወደ ጅቡቲ በሹፍርና ስራ ወስደውታል።

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ሀብቶም ባገኘው አጋጣሚ ተደስቶ ወደ ጅቡቲ ያቀናው በ2007 ዓ/ም ነው ስራውንም ለ 6 አመት ሰርቷል።

በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ዘመቻ ሲጀመር ሀብቶም በጅቡቲ በመደበኛ ስራው ላይ ነበር። ጦርነቱ የተጀመረው ጥቅምት ውስጥ ነበር።

ለሀብቶም ደግሞ የስራ መልቀቂያ የተሰጠው ህዳር 3 2013 ዓ/ም ነው። ከዛን ሰአት ጀምሮ ሀብቶም ወደ ኢትዮጵያ አልተመለሰም ነበር።

ሀብቶም ከስራ ሲሰናበት መኖር መብላት ስላለበት ጅቡቲ ውስጥ ከሚያውቃቸው ኢትዮጵያውያን ጋር ሆኖ በሹፍርና እና በተለያዩ ስራዎች ውስጥ ያልፍ ነበር።

ከ 20 ቀን በፊት ባለበት አካባቢ የጅቡቲ ፖሊሶች ከኢትዮጵያ የኢንባሲ ሰራተኞች ጋር በመሆን አፍነው አ/አ አምጥተውታል።

አ/አ ሲገቡ የመንግስት ልሳን የሆኑ ሚዲያዎች በሰሜን ዕዝ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ያደረሱት አሸባሪዎች ተያዙ በማለት የሀሰት ዜና ሰርተዋል።

ይሄንን እውነት ማረጋገጥ ከፈለጋችሁ

ሀብቶም ከ 3 አምባሳደሮች ጋር ስራ ሰርቷል ሱሌማን ደደፎ ፤ ሻሚሁን ሻሜቦ ፊታሞ አብዱላዚዝ መሀመድ ጋር ሰርቷል። ይሄንንም ማረጋገጥ ይቻላል።

በተጨማሪ ልመርቅላችሁ ከሀብቶም ጋር የተያዘው ኮነሬል መሀመድ በሪሁ ኮነሬል ሳይሆን ዲፕሎማት ሆኖ አቡዳቢ እና ጅቡቲ የሰራ ለስራ ተጠርቶ ተይዟል።

ስለ ሀብቶም ገብረስላሴ በትክክል ፌስቡኩን ማየት እና ማረጋገጥ ከፈለጋችሁ ይህ የፌስቡክ ስሙ ነው Habtom Gebreslassie.

About Author