ከኖቤል ተሸላሚነት ወደ ጦር ወንጀለኝነት

ከኖቤል ተሸላሚነት ወደ ጦር ወንጀለኝነት

The Nobel committee should resign over the atrocities in Tigray.

ለ 2019 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ 2019 የሰላም ሽልማት የሰጡ የአካል ሁሉም የኮሚቴው አባላት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ጠየቀ።

ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ የተጠየቀበትም ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ በትግራይ ላይ የተደረገው ጦርነት ለወራት ቀጥሏል ፡፡

በዚህም ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል ቆስለዋል ፣ ሴቶችና ልጃገረዶች በወታደራዊ ኃይሎች ተደፍረዋል።

ከ 2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። ህፃናት ሞተዋል አዛውንቶች ሳይቀር ተደፍረዋል።

አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በትግራይ ክልል ከፍተኛ የሆነ ድርቅ አለ ብዙ ሰዎች በርሀብ እየሞቱ ነው። ለዚህ ሁሉ ምክንያቱ የህግ ማስከበር ጦርነት ነው።

ስለዚህ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ አባላት በትግራይ ውስጥ ጦርነትን በማካሄድ ለተከሰሱት ዐብይ አህመድ የ2019 የሰላም ሽልማት የመስጠት ግለሰባዊ ኃላፊነት አለባቸው ፡፡

በማለት The guardian ፅሁፉን ይቀጥላል። አባላቱ በዚህም በኖቤል ኮሚቴ ውስጥ ያላቸውን የክብር ቦታ በመቃወም ስራ መልቀቅ አለባቸው ይላል።

The guardian ሀተታውን ሲቀጥል ኮሚቴው ብሎ ይጀምራል።

“ሰላምን እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማምጣት ጥረት በማድረግ በተለይም ከጎረቤት ከኤርትራ ጋር የድንበር ግጭትን ለመፍታት በቆራጥነት ተነሳሽነት”
የኖቤል ሽልማት መስጠቱ ተገቢ ነበር።

ሆኖም ግን አሁን ላይ የኤርትራ ኃይሎች ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ እና ከአማራ ክልል መንግስታት ኃይሎች ጋር በመሆን ያደረጉትን ዘግናኝ ተግባር ኮንኗል።

በርካታ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመ እልቂት የተገለጠ ሲሆን በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ አስገድዶ መድፈር እንደ ትልቅ መከራከሪያ ጠቅሷል።

ስለ ጦርነቱ አጀማመርም The guardian ጥቂት ጠቅሷል።

ጦርነቱ የተጀመረው ባለፈው ህዳር ሲሆን የፌደራል ወታደሮች ከኤርትራ ኃይሎች ጋር በመሆን ወደ ትግራይ ሲገቡ፤ ሁሉ ሰው የሚያውቀው አንድ ነገር ነበር።

ዓላማው የተመረጠውን የክልል መንግስት እና የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ (ህወሃት) መሪዎችን በአመፅ ለማሰር ነው በሚል ነበር ፡፡

በማለት ስለ ጦርነቱ ካብራራ በኋላ ዘመቻው እጅግ የሚያስጠላ ሆኗል። አሜሪካ ዐብይን በዘር ማጽዳት ወንጀል ተችታለች። በማለት አስቀምጧል።

ይህ ብቻ ሳይሆን በበርካታ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰውንም በደል ፤ አስገድዶ መድፈር የዘር ጥቃት የህፃናትን ሞት አውግዟል።

በተጨማሪም እንደ ሆስፒታሎች ፣ የውሃ ተቋማት ፣ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርስቲዎች ሲቪል ሰርቪስ ሰጪ ተቋማት መውደማቸውን መዘረፋቸውን ጠቅሷል።

አሁን ላይ በትግራይ ክልል ከ 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን የትግራይ ተወላጆች ከ 85% የክልሉ ህዝብ ለመትረፍ እርዳታ ይፈልጋሉ ግን እየደረሰባቸው አይደለም።

በተጨማሪም ከተባበሩት መንግስታት እና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች የምግብ እና የአስቸኳይ እርዳታ ለማስገባት የኤርትራ ወታደሮች እንቅፋት ሆነዋል ይላል ፅሁፉ።

በዚህ ክረምት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በረሃብ የመሞት አደጋ ተጋርጦባቸዋል። ምናልባት በ1985 በነበረ ጦርነት ያየነውን አይነት ዘግናኝ ምስሎች በድጋሚ እናያልን ይላል።

ዘገባው የሰብአዊ መብት ባለሞያዎች ሀሳብ ያቀረበ ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ መንግስት የዘር ማጥፋት ወንጀል እያካሄደ ነው ያሉትንም ጠቅሷል።

በመጨረሻም የ The guardian ፅሁፍ እንዲህ ጠይቋል።

ጠ/ም አብይ አህመድ በገዛ ሀገሩ እና ወገኖቹ ላይ ጦርነትን ሲያውጅ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ ምን አድርገዋል? ስለጠፉ ጥፋቶች ምን ብለዋል?

በዲሞክራሲያዊ መንገድ ባልተመረጠ ስልጣን ላይ ላለው ዐብይ አህመድ መርጠው ሽልማቱን ከመስጠታቸው በፊት አጠቃላይ የአደጋ ግምገማ አካሂደዋልን?

ወይም ይህ በአስተያየት ኮሚቴው አስቀድሞ ሊገምተው ያልቻለው ነገር ነው? እያለ ዘ ጋርዲያን ይጠይቃል።

ባለፈው ዓመት የኖቤል ኮሚቴ በሽልማቱ ላይ የተነሱ ቅሬታዎችን አስመልክቶ ያለውን አቋም በድጋሚ በማሳየት ተሸላሚውን በመከላከል ላይም አቋሙን አሳይቷል።

ይህ ሁሉ ውጥንቅጥ በሀገር ውስጥ ሲሆን የኖቤል ሽልማት የሰጡ ኮሚቴዎች በድጋሚ ነገሮችን ለማጤን አሁንም ምንም አይነት ፍላጎት አላሳዩም ብሏል ዘ ጋርዲያን።

ዘ ጋርዲያን የፅሁፉን ሙሉ ሀተታ ሲያጠቃልም በ 2019 የኖቤል ተሸላሚ አድርጎ የመረጣቸው ጠ/ም ዐብይ አህመድ ትልቁ ስህተት እንደሆ ዘግቦ ሀተታውን አጠቃሏል።

እኔም የ ዘጋርዲያንን ሀሳብ ለኛ መሀበረሰብ በሚስማማ እና ሁሉም በሚገባው መልኩ ቀለል ባለ አማርኛ እንደዚህ አቀረብኩላችሁ ሰናይ ቀን።

About Author