ABOUT ME

አቶ ተስፋዬ ሰሙንጉስ እባላለሁ። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ  ከ April 17, 2015 ጀምሮ

ላለፉት 7 አመተታ በተለያዩ ዘርፎች ማህበረሰባችንን በቅንነት በነፃ እያገለገልኩኝ እገኛለሁ።

በተለይ ደግሞ “ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ፍፁም በጎነት ነው ”

በሚል መሪ ቃል በርካታ የቴክኖሎጂ ትምህርቶችን ለማህበረሰቤ

ዘር ፤ ብሔር ፤ ሀይማኖት ሳይገድበኝ የማውቀውን አሳውቄአለሁኝ።

አሁንም ባለኝ ትርፍ ጊዜ የማውቀውን በማሳወቅ ላይ እገኛለሁ።

በፈረንጆች ከ 2018 ወዲህ ደግሞ ማወቅ መልካም ነው የሚለውን አቋሜን

በሀይማኖት ፤ በፖለቲካ ፤ በቴክኖሎጂ ፤ በብዙ ማህበራዊ ተሳትፎ በሚያስፈልጋቸው

ተሳትፎዎች ላይ ሁሉ በመሳተፍ በፅሁፍ ፤ በቪዲዮ ፤ በተለያዩ ዘመኑ ባፈራቸው

የማህበራዊ ሚዲያዎችን መንገዶች በመጠቀም ሀሳቤን በነፃነት በተለይ ለትውልድ ሀገሬ

ይጠቅማል የምለውን ሁሉ ማንነትን ፤ ብሔርን ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሳልደግፍ በግል የተሰማኝን

መልካም ነገር ብቻ በማቅረብ ህብረተሰቤን በማገልገል ላይ የምገኝ በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ደግሞ ካናዳዊ የሆንኩኝ ግለሰብ ነኝ።