በአለም መድረክ በድጋሚ ተዋረድን

በአለም መድረክ በድጋሚ ተዋረድን

የአምባሳደር ፍፁም አረጋን ኢንተርቪው ሰማሁት አቶ ንአምን ዘለቀ በፈረንሳይ ቴቪ ጣቢያ በአደባባይ እንዳዋረዱን አቶ ፍፁም አረጋ በ CNN ደገሙት።

ጥቂት ከተሳቀኩበት ክፍል ልጀምር

ጋዜጠኛ Zain Asher ( CNN ):- እንዴት ነው በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰውን justify ልታደርጉ የምትችሉት?

Fitsum Arega:- የኢትዮጵያ አምባሳደር በዋሽንግተን ዲሲ የሚባለው ሁሉ የውሸት propaganda ነው።

Zain Asher ግራ ገብቷት የራሳችን reporter ቦታው ድረስ ሄዳ ከአንድ ቤት 7 የሞቱበትን በየሆስፒታሉ ተደፍረው የወደቁትን, የደረሰውን ሁሉ በማስረጃ አይተናል እኮ

Fitsum Arega:- የኢትዮጵያ አምባሳደር በዋሽንግተን ዲሲ እንዳልኩት ማስረጃ የሌለው ውሸት ነው።

ጋዜጠኛ Zain Asher ( CNN ):-ግራ ገብቷት ደንግጣ ታየዋለች። ይሄኔ እኔ በሰቀቀን ክው ብዬ ኢንተርቪውን ማየት ቀጠልኩኝ።

አንዳንዴ እኮ ሁሉን ነገር ዋሽቶ መኖር የግድ አይደለም። እርግጥ ከዚህ ውጪ አዎትክክል ነው ብለው ማመን አለባቸው ብዬ አላምንም።

ነገር ግን ቢያንስ አለም የሚያውቀውን እውነት ጠ/ም አብይ አህመድ በፓርላማ ያመኑትን ቃል በቃል እንቀጣለን ያሉትን በድጋሚ ማለት ይቻላል።

በጦርነት ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ አንዳንድ ነገሮች ተከስተዋል እኛም ይህ ጉዳይ እንደ ሀገር እና እንደ ህዝብ ተሰምቶናል በማጣራት ላይ ነን ይባላል እኮ።

ወይም ደግሞ በእርግጥ የተፈጠሩ ነገሮች አሉ ከሚባለው በላይ ተጋኗል አሁን እኛ ባለን መረጃ መሰረት ችግሮችን በየፈርጁ እየፈታን ነው ይባላልም።

ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ ከኤዢያ እስከ መካከለኛው ምስራ ከአፍሪካ እስከ ካሬቢያን ሀገሮች የተሰማን እውነት በጠራራ ፀሐይ መካድ ነውር ነው።

ሌላው ይህ ትልቅ ሀገራዊ ክስረት የዲፕሎማሲያችንን መዋረድ የሚያመለክተውን ኢንተርቪው አይተው አምባሳደሩን ያሞካሹት ገርመውኛል።

ሀገር እና ህዝብ እኮ ይቀጥላል። መንግስት እና የመንግስት ባለስልጣናት ያልፋሉ። ታዲያ ዛሬ ላይ ባለስልጣናት የማይሻር ስህተት ለምን ይሰራሉ?

እውነትን መቀበል እኮ ለትውልዳችን የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳ አይደለም ትውልዱ ዛሬ በደንብ ነቅቷል በደቂቃ መረጃ ያገኛል ለምን ይሄን ትውልድ እንዋሸው?

ብዙ የተማሩ የሚያገናዝቡ ወጣቶች እኮ ሀገራችን አሏት። ይህ ሁሉ ባለበት ሀገር ላይ ሆድ አደር ካድሬዎች እንዴት በትውልድ ይቀልዳሉ?

ለማንኛውም አምባሳደር ፍፁም አረጋ ፤ ነገር አሳምራለሁ ብለው የባሰ ነገር አበላሽተዋል። አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስትን ጭምር አዋርደዋል።

ለቦታው ፈፅሞ ይመጥናሉ ብዬ አላምንም። እርግጥ ብዙ የሰሯቸው ስራዎች እንዳሉ ቢሰማኝም እንዲህ ቀሽም ስህተት ሲሳሳቱ ደግሞ ያሳፍራል።

About Author