ይህ ህዝብ እኮ ያሳዝናል

ይህ ህዝብ እኮ ያሳዝናል

ቀበሮ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል ዋለች። እየተባለ የሚመሰል ምሳሌ አለ። አሁን ላይ ያለው ህዝብም እንደ ቀበሮ እየሆነ ያለ ይመስለኛል።

ከዛሬ 30 አመት በፊት ጀምሮ ይህ ህዝብ የሆነ ነገር ይወድቅልኛል ፤ አገኛለሁ ፤ እበላለሁ ፤ ያልፍልኛል እያለ በተስፋ የሄደውም የመጣውም እያጓጓው ይኖራል። በዘመነ ኢህአዴግ ጊዜ የንብ ቲሸርት አስለብሰው የተስፋ ማር ሲያስልሱት የነበሩ ሰዎች ዛሬ ደግሞ አንፖልን አስጨብጠው በጭለማ እየጋለቡት በባዶ እየተጫወቱበት ነው። አንዱ ካድሬ ዛሬስ ምን ሰራህ ተብሎ ሲጠየቅ የሰራውን ሪፖርት ለማድረግ አንፖልን በዳቦ አሰርቼ ዳቦው ተባርኮ ፎቶ ከተነሳንበት በኋላ ዳቦው ተበልቷል ይላል። ሌላኛው ካድሬ ደግሞ አንተስ ምን ሰራህ ሲባል በርካታ አህዮች ላይ የጠ/ም አብይ ፎት አድርገን ከተማውን ዞረናል ይላል። (አህዮች የምትለዋ ይሰመርበት) ሴት አባል የሆነች የብልፅግና ካድሬ አጨብጫቢ ደግሞ አንቺስ ምን አደረግሽ ስትባል ሴት አባሎቻችን በብልፅግና ጊዜ በሻማ ሳይሆን በአምፖል ይወልዳሉ ትላለች።

ብቻ ምን አለፋችሁ የመንግስት ካድሬዎች ለራሳቸው ከርስ ሲሉ ምንም በማያውቀው ህዝብ ይጫወቱበታል። ወደ ፈለጉትም አቅጣጫ ይዘውሩታል።(ህሊናቢስነት ይባላል) ይህ ህዝብ ግን ኑሮው ፈቀቅ ሳይል መንገድ ሳይሰራለት ሆስፒታል ሳይገነባለት ትምህርት ቤት ሳይመሰረትለት ሌላ መንግስት ይመጣል። የሚመጣውም ይጫወትበታል። አዲስ መጪው በላተኛው መንግስትም ሌላ አጀንዳ ይዞ ይመጣባቸዋል። የቀድሞ መንግስት ምንም አልሰራላችሁ እኛ ደግሞ ወተት እናዘንባለን ብሎ ይገለጣል። በዚህ ምስል ላይ ያሉት ምስኪን ኢትዮጵያውያንን ተመልከቱ ሁሉ ተስፈኞች ሆነው እንጂ ብልፅግና እና አንፖል ገብቷቸው አይደለም ሊገባቸውም አይችልም። ወደዚህ አዳራሽ ሲጠሩ የተጠሩት በሚፈልጉት ነገር አጓጉተዋቸው እንጂ አሁን ያለው ፖለቲካ ገብቷቸው አይደለም። ሊገባቸውም አይችልም ምክንያቱም ምንም ስለሌለው። ለማንኛውም ፈጣሪ ለዚህ ድሀ ህዝብ እና ሀገር ዘንበል ይበልለት እንጂ የመንግስት ካድሬዎች የሚሰሩት እጅግ የሚያሳፍር ተግባር ነው። በጣም ያሳዝናል። ልክ እንደ ቀበሮዋ ከዚህ የማይረባ ፖለቲካ የሆነ ነገር ይወድቅልሀል እያሉ ወደፈለጉት መንገድ በባዶ እየመሩት ይገኛል ለዚህም ህዝብ ፈጣሪ ልቡን አይቶ ይጎብኘው አሜን።

About Author