የተንጠለጠለች ተስፋ

የተንጠለጠለች ተስፋ

የተንጠለጠለች ተስፋ ወይ ወድቃ ትጠፋለች ወይም ወድቃ ትሰፋለች! የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችን ደጋፊ እና ተቃዋሚ ስመለከት የሚያስፈራኝ ነገር አለ።

አብዛኛው በ2 ጎራ የተከፋፈሉት ደጋፊ እና ተቃዋሚ ተስፋ የሚያደርጋቹው በቁጥር 1 እና 2 የሚባሉ ሰዎችን እና አመራራቸውን ነው።

በንደዚህ አይነት ሰዎች ላይ መደገፍ ዛሬ ደስታ ሊሰጥ ይችላል። ለመፅናናትም ምክንያት ሊሆን ይችላል ግን የሚያስመካ የሚያስኮራ አይደለም።

የተስፈኞች ተስፋዎች (ከብልፅግና)

ብዙ መንግስትን የሚደግፉ ለመንግስት ከጠዋት እስከማታ አሸወይና ወይና የሚያዜሙ ሰዎች አብይ አህመድ ዋናቸው እና ተስፋቸው ነው።

ስለ አብይ አውርተው አይጠግቡም በሱ ከመጣህባቸው በአናትህ ሊሰነጥቁ ይፈልጋሉ ወይም በስድብ ይሰነጣጥቁሀል እያደረጉትም ነው።

የተስፈኞች ተስፋዎች (ከህውሓት)

በሌላኛው ጎራ ደግሞ ሁሉም አቅሙን አሟጦ ጌታቸው ረዳ የኔ ሲኒታይዘር እያሉ ሌት ተቀን ከበሮ ሲደልቁለት ሲያሞግሱት ይታያሉ።

ወይም ደፂን እንደማይነቀነቅ አለት በመቁጥር የተስፋቸው ሁሉ ጥግ አድርገው ሲያወሩ ታያላችሁ እያደረጉትም ነው።

የተስፈኞች ተስፋዎች (ከኦሮሞ ግንባር)

ሌላው ጀዋር ከእስር ሲፈታ ሁሉ ነገር ይቀየራል ግፈኞችን ለዘላለም አናያቸውም በቅርቡ ታሪክ ይቀየራል ብለው የሚያምኑ አሉ።

ጫካ ለጫካ ደግሞ እየተንከራተቱ ጃል መሮን ተስፋ አድርገው መጣን ደረስን ምናም እያሉ ጃስ የሚሉ አያሌ ናቸው።

የተስፈኞች ተስፋቸው (ከጎረቤት ሀገር ኤርትራ)

ኤርትራውያን ከኢሳያስ ውጪ ተስፋ የሚያደርጉት አንዳችም ሰው የለም። ኢሳያስ አንድ ነገር ቢሆን ሀገሪቱንም ህዝቡንም ዋጋ ያስከፍላል።

ኤርትራውያን በሀገራቸው በአስተሳሰቡ ከአለም ጋር የሚራመድ ሀገሪቱን ያላትን ምርጥ ነገር ወደ ሀብት የሚቀይር ሰው አልፈጠሩም።

ምናልባት ጥቂት የማይባሉ በውጪ ያሉ ኤርትራውያን የተሻለ አስተሳሰብ ልብ አላቸው ግን ከኢሳያስ ተሽለው መውጣት አልቻሉም።

የኔ ትልቁ ስጋት እና ተስፋ ቢስነት።

የተንጠለጠለ ተስፋ ያላቸው ተስፈኞች ሆነው ይሰሙኛል። ይህ በቋፍ የተንጠለጠለ ተስፋቸው ወድቆ ሲሰፋ ወይ ሲጠፋም ይታየኛል።

ዛሬ ነገሮች ተለውጠዋል የራሳችሁ ብዙ ጀግና መፍጠር ሲቻል በጥቂት ሰው ላይ መንጠልጠል ጥሩ አይደለም።

አብይ ሰው ነው ነገ ሊሞት ይችላል። ጌታቸውም ደፂም ጀዋር ሊሞቱ ይችላሉ በነሱ መታመን አደጋው የከፋ ነው።

ስለ ሀገር እያሰብን በነዚህ ጥቂት ሰዎች ከተንጠለጠለው ተስፋችን በላይ እኛ በመነጋገር እውነተኛ ጀግና መፍጠር ይሻለናል።

ተስፋ የምናደርጋቸው አብዛኛዎቹ ከሀገር ጥቅም በላይ የግል ስሜታቸውን የሚያስቀድሙ እንደሆኑም ልንረዳም ይገባል።
ልብያለው ልብይበል!
በተንጠለጠለ ተስፋ ላይ ሆነን ብዙ አናፏጭ ይልቅ እኛም ከእንቅልፍ እንንቃ ሁሉም ስጋ ለባሽ ናቸው። እንንቃ!

About Author