የመንግስት አንደኛ ጠላት

የመንግስት አንደኛ ጠላት

መንግስት በፕሮፖጋንዳ እና በሚዲያ ላይ ህዝብን ያደነዝዝለኛል ብሎ አስቦ ቀለብ ሰፍሮ ካሰማራቸው ሰዎች መካከል የመንግስትን ስራ እያልበላሸ ያለው ሰው ማለት ይሄ ነው።

ዛሬ ላይ ነገሮች በቋፍ ባሉበት ሰአት የተረሱ የቆዩ ለማንም ቢሰሙም ሆነ ቢወሩ የማይጠቅሙ ሀሳቦችን እያነሱ መጨቃጨቅ ጥቅሙ ምን ይሆን?

ይህ ሰው አውቆትም ይሁን ሳያውቅ ከሚያወራው ነገር የተነሳ ብዙ ሰዎችን ለቂም ለበቀል እና ለጥላቻ እያነሳሳ ይገኛል።

በተለይ ደግሞ ፖለቲካውን ለማወሳሰብ አሁን ድረስ በተለያየ ሞያ ላይ የተሰማሩትን ሰዎች ስም እየጠራ የሚለጥፈው ስም ለመንግስት ከባድ ነው።

ከህውሓት ጋር የነበረውን ቂም መሰረት አድርጎ በእያንዳንዱ ፖለቲካዊ ሀሳቦች ላይ ህዝብ የበለጠ የትግራይን ንፁሃን እንዲጠላ ማድረጉ መንግስትን ዋጋ ያስከፍለዋል።

በቅርቡ እንኳን ጠ/ም አብይ ደውለውልኛል እያለ ስም እየጠቀሰ የሚያወራውን እንደ ትልቅ ጥሩ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። ሀሳቦቹ የመንግስት አቋም ስላልሆኑ።

ዛሬ ላይ የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ ርሀብ ላይ እያለ እንኳን እወደዋለሁ አዝንለታለው ለሚለው ህዝብ ሳይራራ አሁንም ተራ ወሬ በማውራት ተጠምዷል።

ለኔ በግል የሚገባኝ ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋ ማርያም ማለት መንግስት አሁን በትግራይ ክልል ላይ ሊሰራ ያሰበውን ስራ ሁሉ ያደናቅፋል ባይ ነኝ።

ሌላው ደግሞ ፈፅሞ ሚዲያ ላይ መወራት የሌለባቸውን ነገር በማውራት የቆየ ቁስል የቆየ ቂም ሰዎች እንዲያስታውሱ በማድረግም ውጥርት እንዲነግስ እያደረገ ነው።

በብዙ ነገር ወደፊት በመሄድ ሲቻል ሰላማዊ በሆነ መንገድ ነገሮችን እንኳን በንግግር በድርድር ወደ ሰላም ይምጡ ቢባል እንኳን ከዚህ ጋዜጠኛ የተነሳ ነገሮች ከረዋል።

ዛሬ አዲስ ቀን ነው! ወደኋላ 30 አመት እየተጓዝን የገዛ ቂማችንን በቀላችንን የውስጥ ፍላጎትን ብቻ እያዳመጡ ዛሬን ማበላሸት ለማንም አይጠቅምም።

ከዚሁ ጎን ለጎን መንግስት ይሰሩልኛል ያላቸው በርካታ አክቲቪስቶች የመንግስት ደጋፌ ሚድያ ላይ ፕሮፖጋንዳ ሰሪዎች አሁን ብዙ ነገር እያበላሹ ነው።

በቅርቡ እንኳን ስዩም ተሾመ በጭራሽ መወራት እና መነገር የሌለበትን ለመንግስት ሲሰሩ የነበሩ ጓደኞቹን ሳይቀር እንዴት የሀሰት መረጃ እንዳሰራጪ ተናግሮ ነበር።

ታዲያ መንግስት እንደነዚህ አይነት ሰዎችን ስለምን ብሎ ዝም ይላቸዋል? ስለምንስ ሚዲያ ላይ ቀርበው የበለጠ እንድንባላ ለማድረግ ፍቃድ ሰጣቸው?

ምናልባት መንግስት እኛ ሰላም መሆናችንን አይፈልግም ይሆን? ምናልባት በነዚህ ሰዎች ውስጥ ሆኖ እንድንባላ እየሰራ ይሆን? በጣም ግራ ገብቶኛል።

About Author