ከሳኡዲ አረቢያ የተሰማው ጉድ።

ከሳኡዲ አረቢያ የተሰማው ጉድ።

ተስፍሽ በሳኡዲ ስላለው ነገር ከ አላህ በቀር ከማንም መፍትሄ የለም። የኢትዮጵያ መንግስት የአለም መንግስታት ምንም ማድረግ አይችሉም።

ለምን መሰለህ ከኢንባሲ በር ላይ ሳይቀር ነው ሲው እየታፈሰ ያለው። የመኖሪያ ፍቃድ ያለው ሁሉ ይታፈሳይል ይታሰራል።

እኔ ከስራ ወደቤት ስሄድ ነው ወደ ፖሊስ ጣቢያ የወሰዱኝ ፖሊስ ጣቢያ ስደርስ ሰው እንደ አፈር በየቦታው ተኝቷል ግማሹ ደንግጦ እያለቀሰ ነው።

በየተራ እያስገቡ ፍቃድህን እያዩ ከዛ መልሰው ያለምንም ምክንያት 6 ሰአት በላይ ያስቀምጡሀል።

ተስፍሽ ከ አሁን አሁን ምን ይሉኛል እያልኩኝ በንጋታው እንደገና 3 ሰአት አቆይተው ለቀውኛል።

ፍቃድ የሌለውን ግን እስር ቤት እያጎሩ በጭንቅላታቸው ይጫወቱባቸዋል። ምን እንደተፈጠረ ማንም አያውቅም። ምን እየሰሩ እንደሆነ አይታወቅም።

ተስፍሽ ምናልባት ላትቀበለኝ ትችላለህ ግን እኔም ሆንኩኝ ብዙ ሰዎች የሚያምኑት ይህ መሆን የጀመረው የግብፁ ፕሬዝዳንት ሳውዲ ከመጡ ከ 2 ቀን በኋላ ነው።

እዝህ ያለውን ሰው በማሸማቀቅ ወደ ሀገር ቤት በመላክ ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲነሳ ለማድረግ ውጥረት ለመጨመር ነው።

በተለይ ደግሞ አሁን የምርጫ ጊዜ ስለሆነ አብዛኛው ሰው በመንግስት ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ ይመስለኛል።

እንደነገርኩህ ነው ካላመንከኝ ይሄን መልእክቴን አትፖስተው ካመንከኝ ግን ምንም በፖለቲካ አቋም ብንለያይም ኢትዮጵያዊ ከሆንክ ፖስተው።

ህዝቡ እንዲነቃ ፤ እንዲጠነቀቅ ፤ በዚህ ጊዜ አንድ እንዲሆን እንዳንበታተን ለኢትዮጵያ ህዝብ ይሄን አስተላልፍልኝ አመሰግናለሁ። ሙና ከሳውዲ

እኔም ማን ያርዳ የቀበረ ማን ይናገር የነበረ በሚለው አባባል መሰረት የእህታችን ሙሉ ንግግር በዚህ መልኳ አቅርቤላችኋለው እንደ እምነታችሁ ፀልዩ። መልካም አርብ።

About Author