ልደቴን በመስቀል አደባባይ

ልደቴን በመስቀል አደባባይ

ወዳጄ የተፈወሰ ልብ እና አእምሮ ካለህ እጅግ ሲበዛ ፅንፈኛ ካልሆንክ በስተቀር በመስቀል አደባባይ አይደለም ሚሊዮን ተከታዮች ያሉት ጨዋውን የሙስሊም ማህበረሰብ ቀርቶ ተራው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አስቀድሞ እስካሳወቀ ድረስ በየቀኑ ልደቱን ሁሉ መስቀል አደባባይ የማክበር መብት አለው። ወዳጄ የማወራው ፖለቲካ አይደለም። የማወራው አንድ ዜጋ በሀገሩ ቀረጥ እየከፈለ ለህግ ሁሉ ተገዢ ሆኖ እስከኖረ ድረስ በየትኛውም ቦታ የመሰብሰብ የመፀለይ የማምለክ ሙሉ መብት አለው። ይህ ማንም የሚሰጠው እና የሚነፍገው ጉዳይ አይደለም። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈስን ወሃ አሊያም የሚዘንብን ዝናብ ዘንቦም ወንዝ የሆነን ውሃ የእኔ ብቻ ነው ማለት አይቻልም። ልክ እንደ ዝናቡ እንደ ወንዙ ሁሉ የጋራ በሆነው ሀገራችን ላይ አደባባዮች መንገዶ ሰማይ ምድሩ ሁሉ የሁላችንም የጋራ ንብረቶቻችን ናቸው። ባልተሰለጠነ ጥቂቶች ኢትዮጵያን በገዙበት እንደ ግል ንብረታቸው ህዝቡን እና ሀገሪቱን በሚቆጥሩበት ጊዜ የወጣ አዋጅ እና የባለቤትነት መብት ፋይል እያወጣን የምንከራከር ከሆነ በአንድ ሀገር ላይ 1ኛ እና 2ኛ ዜጋ አለ እንደማለት ነው። ስለዚህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሀገሩ ላይ እኩል መብት ስላለሁ የትኛውም ሙስሊም አይደለም በዚህ በፆም ወቅት ቀርቶ በሳምንት 1 ቀን በእለተ አርብ በየሳምንቱ መስቀል አደባባይ መስገድ ቢፈልግ ሀገሩ እስከሆነ ድረስ ይሄን ያህል መብት አለው። ሌሎችን እስካላፈናቀለ በሌሎች እምነቶች ላይ ጣልቃ እስካልገባ ድረስ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች የማምለክ የመሰብሰብ መብት አለው። አክሱምን ጨምሮ አራት ነጥብ። ወዳጄ አንድ ነገር ልጨምርልህ እና ልጨርስ። ዛሬ በገዛ ሀገሩ ሙስሊሙ አታፈጥርበትም የተባለው ቦታ ላይ የቦምባርሊ ልደት ተከብሮበት ነበር። ታዲያ የቦምማርሊ ልደት በተከበረበት አደባባይ አንድ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም አይደለም ፆሙን ማፍጠር ቀርቶ ልደቱን ማክበር ይችላል።

About Author