አቶ ንአምን ዘለቀ አዋርደውናል

አቶ ንአምን ዘለቀ አዋርደውናል

ዛሬ በአንድ ነገር አፍሬአለሁኝ በአንድ ነገርም ተገርሜ አምሽቻለሁ። መቀመጫውን ፈረንሳይ ፓሪስ ያደረገው THE DEBATE በተሰኘ

በቀጥታ ከፈረንሳይ ፓሪስ ከሚተላለፍ አንድ ትልቅ የቴሌቪዥን ልዩ ፕሮግራም ላይ 3 በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ለክርክር የተጋበዙ ግለሰቦችን አይቼ ነበር።

እነዚህ 3 ግለሰቦች የሚከተሉት ናቸው።

1ኛ MEAZA GIDEY (activist)

2ኛ NEAMIN ZELEKE (Global eth . advocacy Nexus)

3ኛ HENOK GABISA (Fmr.President Oromo Studies Assoc)

እነዚህን በፖለቲካ አቋማቸው እጅግ የተለያዩ ሰዎችን FRANCE 24 በ እንግሊዘኛ በወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ላይ አከራክሯል።

በዚህ ክርክር ላይ በርካታ ነገሮች የተዳሰሱ ሲሆን ሁሉንም በዚህ ፅሁፍ መዳሰስ አሰልቺ ስለሆነ ትቼዋለሁ።

እኔን ግን በጣም ያሸማቀቀኝ የአቶ ንአምን ዘለቀ የክርክር አካሄድ እና ንዴት በተለይ ደግሞ መረጃዎች ላይ ያልተመሰረቱ መረጃዎች አበሳጭተውኛል።

አቶ ንአምን ልክ እንደ ፌስቡክ የላይቭ ስርጭት እንደሚያስተላልፍ ተራ ሰው በአንድ ትልቅ ስመጥር ሚዲያ ላይ መረጃ የሌለው ነገር ማቅረብ ነውርም አሳፋሪም ተግባር ነው።

ሌላው እጅግ አሸማቃቂው ነገር ደግሞ አቶ ንአምን ዘለቀ ምንም አይነት የሚዲያ አጠቃቀም እና ፕሮቶኮል አለማወቃቸው ነው። ለራሳቸውም ሆነ ለሚከራከሩለት መንግስት ክብር አሳጥተውታል።

ውስጣቸው እውነት እንኳን ቢኖር ሲያሳዩት የነበረው ያልተገባ ነገር በጣም አሳፋሪ ሆኖ በግል ታይቶኛል።

(ይህ የእኔ እይታ ብቻ ሳይሆን ታዋቂው የፈረንዳይ ቲቪ ጋዜጠኛ (François Picard (journalist) በመሀል እየገባ ሲያርማቸው ታይቷል።

በመጨረሻ ላይ እጅግ ያሸማቀቀኝ ትልቁ ነገር

በዚህ ክርክር ላይ በተለይ 29፡57 ሰከንድ ላይ አቶ ንአምን ዘለቀ የሚናገሩት ንግግር ምንም መረጃ የሚባል ነገር የላቸውም።

ከግብፅ ጋር የትግራይ አመራሮች እየሰሩ ነው።ይሄም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለመበታተን እንደሆነ በመሀል እየገቡ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

አቶ ንአምን ዘለቀ ይሄን ለመናገር የተጨበጠ መረጃ አግኝተው ይሆን? በአንድ ትልቅ ሚዲያ ላይ ያወሩት ወይስ በፓልቶክ እና በፌስቡክ የሚወራውን ይዘው መጥተው ነው?

በእርግጥ እኛም እሳቸውም የሚያውቁት አንድ እውነት አለ እርሱም ከዚህ ቀደም 500 ሺህ ዶላር ከግብፅ እርዳታ ማግኘታቸው።

ይህ ዜና እነ አቶ ንአምን ዘለቀ በኤርትራ በኩል በርሀ ገብተው ኢትዮጵያን ለማተራመስ መስራታቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው።

አቶ ንአምን የዘላለም ጠላት ከሆነች ከግብፅ ጋር ሲደራደሩ እውነት ከልብ ኢትዮጵያን ለመጥቀም ነበር? (ይህ ዜና በኢሳት 100% በግዜው ቀርቦ ነበር)

እናም አቶ ንአምን ዘለቀ ስሜታቸውን ሳይገሩ በእውቀት ሳይዳብሩ የንግግር ስርዓት የክርክር ደንቦችን ሳያከብሩ በስሜት ተወጥረው መቅረባቸው ስህተት ነው።

በድሮ ታሪክ እና በዘቀጠ የፖለቲካ አመለካከት ተወጥረው እራሳቸውን አብዴት ሳያደርጉ ከመአዛ ጊደይ እና ሄኖክ ጋቢሳ ጋር ለመከራከር መምጣታቸው አስገርሞኛል።

እንደ ግለሰብ እራሳቸውንም እንደ ሀገር ደግሞ ኢትዮጵያንም የኢትዮጵያን መንግስትንም አንገት አስደፍተዋል።

እደግመዋለሁ አቶ ንአምን ዘለቀ ያለ እውቀት በትልቅ ሚዲያ ላይ ቀርበው አሳፋሪ ተግባም አድርገዋል። በድጋሚ በአለም መድረክ አዋርደውናል።

About Author