ሰባተኛው ንጉሥ ይሄን አድርጎ ቢሆን ኖሮ

ሰባተኛው ንጉሥ ይሄን አድርጎ ቢሆን ኖሮ

ሰባተኛው ንጉሥ እናታቸውን እንደሰሙ ሁሉ ንጉስ ከሆኑ በኋላ ጀዋር መሀመድን

ሰምተው ቢሆን ኖሮ ዛሬ ሀገሪቱም እሳቸውም እንዲህ ማጥ ውስጥ አይገቡም ነበር።

ሰባተኛው ንጉሥ የማያውቁትን ኢሳያስ አፎርቄን ከሚሰሙ ይልቅ በቅርብ አዲስ አበባ ያለውን

ልደቱ አያሌውን ሰምተው ቢሆን ኖሮ እንዲህ እንቅልፍ አያጡም ነበር።

ሰባተኛው ንጉሥ ወደ ስልጣን ሲመጡ ዳንኤል ክብረትን ከሚሰሙ ይልቅ ተቀናቃኛቸውን አቶ

አንዷለም አራጌን ሰምተው ቢሆን ኖሮ እንዲህ በየቀኑ ባልባከኑ ነበር።

ሰባተኛው ንጉሥ ብርሀኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው ፅጌን ከሚሰሙ ይልቅ የቅርብ ጓደኛቸው አቶ

ለማ መገርሳን ሰምተው ቢሆን ኖሮ እልፍ የኦሮሞ ህዝቦች ባልከዷቸው ነበር።

ሰባተኛው ንጉሥ ለራሳቸው ስልጣን ሲሉ የቀድሞ የደህንነት መስሪያቤቱን በአሻጥር ባይበትኑት

ኖሮ ዛሬ የግብፅ የሱዳን የማንም ሀገር መጫወቻ አይሆኑም ነበር።

ሰባተኛው ንጉሥ ባጫን ብርሀኑ ጁላን አበባውን ከሚያምኑ ይልቅ አምባቸውን አሳምነውን

ሳአረን ገዛኢን ባያስገድሏቸው ኖሮ ከ100 ሺህ በላይ ህዝብ አያልቅም ነበር።

ሰባተኛው ንጉሥ ደመቀ መኮንን አገኘው ተሻገርን ከሚያምኑ ስልጣን ከሚሰጡ ይልቅ

ሲበዛ ቅን የሆነውን ደብረፂሆንን ጓደኛ አድርገው ቢሆን ኖሮ እንዲህ ባልተጫወቱባቸው ነበር።

ሰባተኛው ንጉሥ ሽመልስ አብዲሳን የኦሮሚያ ፕ/ት አድርገው ኦሮሚያን እንዲህ የሙስና ሜዳ ከሚያደርጓት ይልቅ

የኦነግ ፕ/ሮ መራራ ጉዲ እና አቶ በቀለ ገርባን ቢያስቀምጡ ኦሮሚያ ሰላም ሆና ደም ባልፈሰሰ ነበር።

ሰባተኛው ንጉሥ ለሆዳቸው ያደሩ ሆድ አደር የኢሳት ጋዜጠኞችን በዙሪያቸው አድርገው በየቀኑ

የሀሰት ወሬ ከሚያሰሟቸው ይልቅ 360 ሚዲያን ቢሰሙ ኖሮ አንድ ደረጃ ከፍ ባሉ ነበር።

ሰባተኛው ንጉሥ እጅግ ሞኝ ባይሆኑ ኖሮ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን አስቀምጠው አለም ከሚስቅ ይልቅ

ጌታቸው እረዳን ቦታው ላይ ቢሆን ኖሮ የዲፕሎማሲ ክብራችን 10 ደረጃ ባደገ ነበር።

ሰባተኛው ንጉሥ ምርጫ ቦርድ ወ/ሪት ብርቱኳንን ከሚሰሙ ይልቅ በትግራይ በትክክለኛው ጊዜ
ምርጫ ያደረገውን የትግራይ ክልል ምርጫ ቦርድን ሰምተው ቢሆን ኖሮ!

ዛሬ ህዝቡ ካርድ ቤቱ ድረስ በልመና ባልወሰደ ነበር። እሳቸውም ደረታቸውን ነፍተው በህዝብ በተመረጡ ነበር።
በመጨረሻ
ምሰባተኛው ንጉሥ ውስጣቸው ያበጠውን የእኔነት ስሜት እኔ ብቻ እኔ ልዩ እኔ እኔ እኔ ብቻ ከሚሉት አባዜ ወጥተው
የኢትዮጵያን ህዝብ የብሔር ብሔረሰቦችን ስሜት አዳምጠው
እሳቸውም ትንሽ ከሚዲያው ገለል ብለው በተማረ ወጣት ሀይል መንግስታቸውን አዋቅረው ቢሆን ኖሮ የት በደረሱ።

About Author