ይህ ለኤርትራዊያን ስድብ ነው

ይህ ለኤርትራዊያን ስድብ ነው

ፖለቲከኛ መሆን ማለት ጭልጥ ብሎ ህሊናቢስነት መሆን ማለት አይደለም።

ህሊናን ለእውነት እያስገዙ ህሊና ያለው ማህበረሰብ መፍጠር እንጂ ሙልጭ ያለ ውሸታም

መሆን በታሪክም ሆነ በህግ ያስቀጣል።

የኛ ፖለቲከኞች ግን ሀገራችንን ለኤርትራ ሰራዊት እና መንግስት አሳልፈው ከሰጡ በኋላ አይን

አውጥተው የውጪ ጣልቃ ገብነትን እንቃወማለን ይላሉ። ኤርትራ እኮ ሀገር ነች።

ኤርትራን እና ኢርትራዊያንን መናቅ ካልሆነ በቀር የውጪ ጣልቃ ገብነትን እየተቃወሙ

ኤርትራን ዝም ማለት ለኤርትራዊያን ትልቅ ውርደት ነው። ኤርትራዊ ሁሌም እንደ ሉዋላዊ ሀገር መቆጠር ይፈልጋል።

የገደል ማሚቱ የሆነ የመንግስት ውታፍ ነቃዮች ደግሞ መልሰው የመንግስትን ህሊናቢስነት ቆይ

ለምን ብለው ሳይጠይቁ የውጪ ጣልቃ ገብነት ይቁም እያሉ እንደ ገደል ማሚቱ ይጮሀሉ።

አንዳንዱ ደግሞ ውጪ ሀገር ሲባል አሜሪካ እና አውሮፓ ብቻ ይመስለዋል። ኤርትራ ውጪ ሀገር አትመስለውም።

ይህ ለኤርትራዊያን ምን ማለት መሰላችሁ? ሉዋላዊ ሀገር አይደላችሁም እንደማለት ነው። ስድብ ነው

About Author