የመንፈስ ቅዱስ መገኘት

የመንፈስ ቅዱስ መገኘት

መንፈስ ቅዱስ በታላቅ ክብር የተገኘበት ትልቅ ውሳኔዎች በአንድነት በአንድ ልብ የተወሰኑበት ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል ደረጃ ቅዱስ ሲኖዲስ ያስደነቀን ቀን ነበር።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሲያስደንቀን የዋለው እንግዲህ ከሞላ ጎደል 7 ትላልቅ ውሳኔዎችን በሰላም መንገድ ብቻ በመወሰን የመንፈስ ቅዱስ መገኘትን አስመስክሯል።

ከውሳኔዎችም መካከል በቅደም ተከተል የሚከተሉት ውሣኔዎቹ ይጠቀሳሉ።

1ኛ የቅብዓት ጳጳሳት ነን ያሉትን አወገዘ (ሁሉም የተስማሙበት ድል)

2ኛ አቡነ ማርቆስን በማንሣት አቡነ ያሬድን የምሥራቅ ጎጃም ሊቀ ጳጳስ አድርጎ ሾሟል ይሄም ሽሙት ፍፁም ከሰር የፀዳ ምደባ ትልቅ ውሳኔ ነው።

3ኛ. መንግስት በመስቀል አደባባይ እና ጃን ሜዳን ጨምሮ ትላልቅ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ በዓላት የሚከበሩበት ስፍራ ላይ ካሳየው ዳተኝነት እንዲነቃ።

መንቃት ብቻ ሳይሆን መዳፈሩን እንዲያቆም በታላቅ ቁጣ ጭምር አስጠነቀቀ፣ አፋጣኝ የሚባል ውሣኔም እንዲሰጥ አሳሰበ።

4ኛ በእምነት ተቋም ስም የቤተ ክርስቲያንን ክብርና ማንነት የተዳፈረ የይዞታን ስም በመለወጥ የተደረገው ጽርፈት በአስቸኳይ እንዲታረም አስጠነቀቀ።

5ኛ. የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን የቆይታ ጊዜ ገደበ እስከ ጥቅምት ብቻ ይቆያሉ። ይሄም አንዱ ትልቁ ውሳኔ ነው።

6ኛ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኃላፊዎች የፈጸሙትን ኢቀኖናዊ ነውር አወገዘ። በቋሚ ሲኖዶሱ በኩል ጉዳያቸው ታይቶ ከኃላፊነታቸው እንዲነሡ አቅጣጫ አስቀመጠ።

7ኛ. የፖትርያርኩን የጉባኤ መክፈቻ ቃል ሙሉ በሙሉ አጸደቀ።

የዘንዶው አፎች አሰፍስፈው ነበረ። አንዳችም ነገር ግን አልተፈጠረም መንፈስ ቅዱስ ዘጋው። ታሪክ ተሠራ። ሲኖዶሳዊ አንድነት እና ፍቅርም ቀጠለ።

About Author