ለመኖር ሲኖር እና ለአላማ ሲኖር

ለመኖር ሲኖር እና ለአላማ ሲኖር

የጌታቸው እረዳ እና የደመቀ መኮንን አለም ከርሶ እና አንበሶ።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደ ተረት የሚነገር ትልቅ ታሪክ ተሰርቷል። ይሄን እውነታኛ ታሪክ ለሁላችንም በሚገባ መልኩ እንዲህ በተረት አቀረብኩላችሁ።

ተረት ተረት
ከ30 አመት በፊት ነው አሉ አንዲት በምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለች። በዚህ ሀገር ውስጥ ስልጣን የነበራቸው ሁለት ሰዎች ነበሩ።

አንደኛው ባለስልጣን ደመቀ መኮንን ይባላል። ሌላኛው ደግሞ ጌታቸው ረዳ ይባላል። እነዚህ ሁለት ባለስልጣናት አንዱ ለጥቅሙ ያደራ አንዱ ለአላማ ያደረ ነበር።

ለጥቅሙ ያደረ ደመቀ መኮንን ሲባል ስልጣን ከመውደዱ የተነሳ ሲልኩት ሲላክ ሲቆጡት ሲሸማቀቅ ሲገርፉት የሚገረፍ እንደ አጋሰስ ሲጭኑት ዝም ብሉ ይጫን ነበር።

ሁለተኛው ባለስልጣን ጌታቸው ረዳ የሚሉት ደግሞ እንደ አጋሰስ እንጫንህ ሲሉት የማይጫን ተቀመጥ ፤ ተነሳ እያሉ ያማያስነሱት የማያስቀምጡት ሰው ነበር።

እነዚህ ሁለት ባለስልጣናት በስልጣን ሲኖሩ ሲኖሩ ከለታት አንድ ቀን ስልጣናቸውን የሚያናጋ አንድ ክስተት ተከሰተ።

ይሄኔ ለመኖር ብቻ የሚኖረው እንደ አጋሰስ ሲጭኑት የሚጫን ደመቀ መኮንን የሚባለው ባለስልጣን በጣም ደነገጠ። የሚያረገው ጠፋው።

ስልጣኑን የሚያሳጣው ትልቅ ለውጥ ፊት ለፊቱ መጣበት ይሄኔ እንደለመደው የስልጣኑ ባለቤት አሁን ማነው? ብሎ አሰበ። እንዴት ተደርጎ እንደሚጫን ያልም ጀመር።

ወደልቡም ለ27 አመት ሲጫንበት የነበረው ብልሀቱ ትዝ አለው ወዲያው አሁን ለመጣው ባለስልጣን ማጎብደድ ጀመረ። እንደ አጋሰስ እየተጫኑ መኖር የለመደው ልቡን ሞላው።

ሲረግጡት ሊረገጥ ተናገር ሲሉት ሊናገር ቁጭ ብድግ ሲያሰሩት ሊሰራ በውርደት ሲያኖሩት ሊኖር ወሰነ ይሄኔ ከድሮው በላይ ስልጣን አገኘ በአጋሰስነቱ ቀጠለ።

ሁለተኛው ባለስልጣን ሲጭኑት የማይጫነው ሰው እንጂ አጋሰስ አይደለሁም ያለው ጌታቸው ረዳ ከነበረበት ክብር ወርዶ ለሚወደው ህዝብ ሲል ጫካ ገብቶ።

ከአፈር በላይ አፈር መስሎ ድሎት የለመደውን ሰውነቱን በርሀ ላይ አስተኝቶ ተዋርዶ ከመኖር መንከራተትን መርጦ ላመንበት አላማ ጫካ ገብቶ አንበርካኪውን ይዋጋል።

በመጨረሻም እነዚህ ሁለት ሰዎች ከርሶ እና አንበሶ ኖረው ኖረው መሞታቸው ባይቀርም አሁን ላይ ግን አንዱ ለሆዱ በቁሙ ሞቶ ከርሶ የሚባል ስም ወጣለት።

አንዱ ደግሞ ለአላማው ሊሰዋ ጫካ ገብቶ ለሚጠሉት የፍርሀት ምክንያታቸው ሆኖ ለሚወዱት የተስፋቸው ሻማ ሆኖ

እየቀለጠ ለሚወዱት እያበራ አንበሶ ተብሎ እስካሁን አለ።

About Author