አሁንስ ደስ አላችሁ? የኔ ጥያቄዎች

አሁንስ ደስ አላችሁ? የኔ ጥያቄዎች

ይቺህ ህፃን የሀገራችሁ ኢትዮጵያ ህፃን ልጅ ነች። መርጣ ሳይሆን ተፈጥራ ነው ትግራይ ላይ የተወለድችው።

እንዲህ ሆና ስትመለከቷት ምን ተሰምቷችሁ ይሆን? አሁንም በደስታ እየዘለላችሁ ጮቤ እየረገጣችሁ ነው?

አሁንም ቅዱሱ መንግስታችን ሺህ አመት ንገስልን አንተ ልዩ የፈጣሪ ስጦታ ነህ እያላችሁ ታወድሳላችሁ?

ይሄንን እና ከዚህ የሚበልጡ ስቃዮች በትግራይ ክልል እያያችሁ እየተመለከታችሁ እንዴት አስችሏችሁስ ዝም አላችሁ?

እንዴት አይነት ልብ ቢኖራችሁ ነው አለም ጦርነት አቁሙ ሰላም አውርዱ ተደራደሩ ከዚህ ወደከፋ አዘቅጥ ትወርዳላችሁ ሲባል መስማት ያቃታችሁ?

ይሄንንስ ሁሉ ጉድ እንዳታስተውሉ ማነው አዚም ያደረገባችሁ? ማነውስ ልቦናችሁን የደፈነው? ይህ ሁሉ ትክክል ነው ብላችሁ ታምናላችሁ?

እስቲ እሩቅ ሳይሆን ከ አምስ እና ከሰባት አመት በፊት በሀገራችሁ የነበረውን አንፃራዊ ሰላም አስቡ ታዲያ አሁን ሀገራችሁ ትክክለኛ መንገድ ላይ ነች?

የስንቱ ቤት በለቅሶ ተሞላ? ስንቱስ ለማያውቀው ጦርነት ልጁን ፤ አባቱን ፤ ወንድሙን ፤ እህቱን ገበረ? ይህ ሁሉ ለኢትዮጵያዊ ይገባዋል?

መጨረሻችሁስ ምንድነው? እናንተ የልቦናችሁ አይኖች የታወሩባችሁ ኢትዮጵያውያን ዛሬስ ምንም አልበራላችሁም? ከተኛችሁበትስ አልነቃችሁም?

ነገሮች እየከፉባችሁ ከድጡ ወደ ማጡ እየወረዳችሁ እንደሆነ ዛሬን እንኳን አይታችሁ ስለምን ከተኛችሁበት መንቃት አልፈለጋችሁም?

ከጦርነት ማን ያተርፋል ብላችሁ ታምናላችሁ? ስለምንስ ሀገራችሁን ምድረ በዳ እንድትሆን ከሚሰራ መንግስት ጋር ለመቆም ወሰናችሁ?

ወንድም ወንድሙን እየገደለ ሀገር ነፃ ትሆናለች ሰላም ይመጣል ብላችሁ ታምናላችሁ? ታዲያ በጦርነት ውስጥ ሰላምን ስለምን ናፈቃችሁ?

መቼስ ይሆን ከተኛችሁበት የምትነቁት? መንግስት አደድቧችሁ ልቦናችሁ እንዳያስብ አይናችሁ እንዳያይ አድርጎ ሲያስቀምጣችሁ እንዴት አሜን ብላችሁ ተቀመጣችሁ?

ወገኔ ጊዜው አሁን ነው መንቃት ካለባችሁ አሁን ንቁ አለም ፊቱን እያዞረብን ነው። ወዳጅ ከማይሆኑ ጋር ወዳጅ ሆነን ከወዳጆቻችን ጋር ደግሞ ጠላት ሆነናንል እንንቃ።

About Author